የቴክኖሎጅ ብዜትና ሽግግር ስራዎችን ለመደገፍ ከተሠየሙ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት ጋር የጋራ ውይይት

የቴክኖሎጅ ብዜትና ሽግግር ስራዎችን ለመደገፍ ከተሠየሙ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት ጋር የጋራ ውይይት ተካሄደ፡፡

ኮሌጁ በሁለት ዘርፎች ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን የመጀመሪያው በኮሌጁ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የእንስሳት እርባታ ሰርቶ ማሳያ(Dairy Farm) የሚያግዝ የሙያ አማካሪ ኮሚቴ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኮሌጁ የቴክኖሎጅ ሰርቶ ማሳያ እርሻ ቦታዎች ላይ የሚከናወኑ የቴክኖሎጅና ምርምር ስራዎችን የሚደግፍ የእርሻ ስራ አማካሪ ኮሚቴ ነው፡፡

በሁለቱም ዘርፎች የተሠየሙት የኮሚቴ አባላት በዘርፉ ተሻለ ልምድና እውቀት ያላቸው መምህራን መሆናቸው ተገልፇል፡፡

ስብሰባውን የመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ሰይድ

ለአማካሪ ኮሚቴዎቹና ስራውን በባለቤትነት ለሚሠሩት የቴክኖሎጅ ብዜትና ሽግግር ቡድን ሠራተኞች ኮሚቴ ለምን ማቋቋም እንዳስፈለገ፣የኮሚቴውን ሚናና የስራ ሀላፊነት፣ቀደም ባሉት አመታት በሰርቶ ማሳያ ቦታዎች ላይ የተሠሩ ስራዎች ጋር በተየያዘ የነበሩ እጥረቶችና ስኬቶች እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይ መነሻ ሀሳብ አቅረበዋል፡፡

በኮሌጁ አካዳሚክ ምክት ዲን አቶ ውቡ ታየ እና በአስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ በዛብህ ይመርም ተጨማሪ ሀሳብና አስተያየት ተሠጥተው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የኮሌጁ የቴክኖሎጅ ብዜትና ሽግግር ስራዎች በጥልቀት ተገምግመዋል፤የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫም ተመላክቷል፡፡

ሀርቡእና መድሃኒአለም የእርሻ ቦታዎች ጋር በተየያዘ በቀጣይ ወራት

በክረምቱ ወራት ያልለሙ እርሻዎች ላይ ጭምር የተሻሻለ የስንዴ ዝርያ በበጋ መስኖ ልማት በጥራትና በስፋት ማልማት ፣ተጨባጭ የሆኑ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን መስራትና ወደ አርሶአደሩም ተደራሽ ማድረግ ፣ስንዴን ጨምሮ በምርምር የተገኙ ምርጥ ዘሮችን የማለማመድና የመሞከር ስራ፣የሀርቡ እርሻ ላይ የሚታይ ጨዋማነትን የመቀነስ ስራ ፣በቴክኖሎጂ የታገዙ የምርምርና የእርሻ ስራዎች፣ የቋሚ አትክልት ልማትን አጠናክሮ ማስቀጠል፣የእርሻውን የጥበቃ ማጠናከርና አጥር የመከለል ስራ፣ከባለ ድርሻዎችና አጋር አካላት ጋር ተቀራርርቦ መስራት…ወዘተ በትኩረት የሚሠሩ ሲሆን

በተመሳሳይም የኮሌጁ የእንስሳት እርባታ ጋር በተየያዘ

ከምርምር ማእከላት ጋር በመነጋጋር የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን የማምጣትና የማለማመድ፣የእንስሳት ጤና አያያዝና አጠባበቅን የማሻሻል ስራ፣ የመኖ እጥረትና ጥራት ላይ ችግር ፈች የሆኑ አዳዲስ አሠራሮችን በጥራት መስራት ፣ የእንስሳቱን ምርትና ምርታማነት በማሣደግ ከእንስሳቱ የሚገኘውን ተዋፅኦ ለከተማው ማህበረሰብ ጭምር በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ ስራ..ወዘተ በዘርፉ

በትኩረት እንደሚሠሩ ከውይቱ ማዎቅ ተችሏል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም ከተደራጀው ኮሚቴ በዘርፉ ላጋጠሙ ችግሮች በጥናት የተደገፈ ሙያዊ እገዛዎችና መፍትሄዎች በስፋት እንደሚጠበቅና ለዚህም የኮሌጁ ማኔጅመንት አስፈላጊውን እገዛና ክትትል ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አቶ ጀማል አሳስበዋል፡፡

ህዳር 01/2015 ዓ.ም

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

Related

Notices

  • Announcements
  • Vacancy
  • Call For Papers
  • Bids

Downloads

  • Registrar
  • Budget and Finance
  • Policies and Legislations
  • Research and Technology Transfer

Partenerships

  • ARSBA
    Amhara National Regional State Bureau of Agriculture
  • Ministry of Labor and Skills
    Ministry of Labor and Skill
  • wollo unversity
    Wollo Unversity
  • SNV
    SNV Ethiopia
  • giz
    GIZ Ethiopia
  • Smis
    Small and Micro Irrigation Support
Archives