የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ በኮሌጁ ለረጅም አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላገለገሉት የኮሌጁ ሰራተኞች የምስጋናና ሽልማት ፕሮግራም በዛሬው እለት አካሂዷል።
የፕሮግራሙ የክብር እንግዶች የወሎ ዩኒቨርሲቲ ላኮመልዛ ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፣ የዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ሽፈራው ፣ በኮምቦልቻ አየር መንገድ ፌደራል ፖሊስ ኮማንደር ይቻላል ተገኝተዋል።
በዚህ ፕሮግራም የተለያዪ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን የኮሌጁ የቀድሞ ዲን አቶ ጀማል ሰይድ እና አስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ ብርሀኑ በየነ በኮሌጅ በነበራቸው ቆይታ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እና የነበራቸውን አጠቃላይ የስራ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በዶክመንተሪ በማዘጋጀት ጥሩ የስራ አጋርነትን፣ ወዳጅነትን ና ጓደኝነትን አስታውሰንበታል።
ባጠቃላይ በዛሬው ውሎ በኮሌጁ ለረጅም አመታት ሲያገለግሉ የቆዩ እና በፍቃዳቸው የለቀቁ፣በአመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩ እና በፈቃዳቸው ከሀላፊነት የተነሱ እንዲሁም ለረጅም አመታት አገልግለው በጡረታ የተገለሉ 15 የኮሌጁን ባለሙያዎች አና አመራሮች በኮሌጁ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በማመስገን የተለያዩ ሽልማቶች እና የምስክር ወረቀት በመስጠት ኮሌጁ ቀሪ ግዜያቸውን ያማረ አድርጎ እድሜና ጤና ሰጥቶ ያቆይልን በማለት በክብር ሸኝቷል።
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ኮ/ግ/ኮ ጥር 27/5/2017