በቃሉ ወረዳ 034 ቀበሌ የሰርቶ ማሳያ እርሻ ላይ በክረምቱ ወቅት የለሙ የስንዴ፣ ጤፍና ቋሚ አትክልቶች በሠራተኞች ተጎበኙ፡፡
-በጉብኝቱ ላይ የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን አቶ ውቡ ታየና አስተዳደር ልማት ምክትልዲን አቶ በዛብህይመር፣ የኮሌጁ መምህራንናየልዩ ልዩ ስራ ክፍል ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
-በእርሻ ቦታው ላይ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በሚመለከት በኮሌጁ አስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ በዛብህ ይመር፣ የቴክኖሎጅ ብዜትና ሽግግር ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ አብዱሮህማን ነጋ፣በኮሌጁ የአግሮኖሚ ባለሙያ በአቶ ፈንታው ሰይድ በኮሌጁ በ2014/2015 በጀት አመት ስለተሠሩ ልማቶች፣ በሂደቱ ስላጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ በተሠሩ ስራዎች ስለተገኙት ስኬቶች፣ በቀጣይም ተጠናክረው ስለሚቀጥሉ የቴክኖሎጅና የምርምር ስራዎች ለሠራተኞቹ በቦታው ላይ ገለፃ ተደርጓል::
-ሥራው በአብዘሀኛው በክረምት ወራትየተሠራ ሲሆን ክረምቱን ተከትሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ ተግዳሮት የነበረ ቢሆንም መሬቱን ለማልማት በነበረ ቁርጠኝነት ችግሮችን ተቋቁመን በማለፍ ያመጣነው አንዱ ስኬታማ ተግባራችን በመሆኑ ለውጤቱ የኮሌጁ ማህበረሰብ እና አጋር አካላትን ሊመሠገኑ ይገባል ሲሉ አቶ በዛብህ አሳውቀዋል ፡፡
-ከስንዴና ጤፉ ጎን በጎን በአረንጓደ አሻራ መርሀግብር የተተከለው ቋሚ አትክልት ተገቢው እንክብካቤ የተደረገለት በመሆኑ በአስተማማኝ ሁኔታ መጽደቁን አቶ በዛብህ በንግግራቸው ጠቅሰው በተለይም አጋር አካላት ጋር በመተባበር ለሰውና እንስሳት ምግብነት በስፋት የሚያገለግለው እንሰትተክል ላይ የተጀመረው የምርምር ስራ ለወሎ እና አካባቢው ትልቅ ተስፋን የሠነቀ እና በስፋት የሚሠራበት መሆኑንም ለተሳታፊዎቹ አስረድተዋል ፡፡
-በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በቀጣይ በሁሉም የኮሌጁ እርሻ ላይ የበጋ ስንዴ በመስኖ ለማልማት እቅድ የተያዘ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተገልፇል፡፡
-ኮሌጁ የጀመራቸውን የቴክኖሎጅና ምርምር ስራዎች በተሻለደረጃ ለማከናወን የክልሉ ግብርና ቢሮ የትርፍ ውሃ ማጠንፈፊያ ሪጀር፣ የፈረስ ጉልበታቸው ከፍተኛ የሆኑ የውሃ መሳቢያ ፓምፖች፣ መከስከሻዎችና መዉቂያዎችን ድጋፍ እንድያደርግም ተጠይቋል።
-ዘንድሮ በእርሻው ላይ አልምተን ያገኘነውን ስኬት ከራሳችን አልፈን ከኛ ብዙ ለሚጠብቀው ማህበረሰባችን የምናሰርፀው ይሆናል፤ ለዚህም የኮሌጁ ማህበረሰብ በተለይም መምህራን ሙያዊ እቅምና ችሎታቸውን ተግባር ላይ በመዋል ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገቡ ምክትል ሃላፊው አሳስበዋል፡፡
-በመጨረሻም የእርሻው ልማት ጋር በተየያዘ ከተሳታፊዎች ጠቃሚ ሀሳብና አስተየየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ
ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት22/2015 ዓ.ም