የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ በተለያዬ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን የደረጃ 4 ተማሪዎች አስመረቀ

           

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር የደረጃ ማሻሻያ የክህሎት ልማት ስልጠና ለቀበሌ ልማት ጣቢያ ግብርና ባለሙያዎች ከመጋቢት 22/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 ወራት በ6 የትምህርት ክፍሎች በሰብል ልማት፣ በመስኖ፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ፣ በእንስሳት እርባታ፣ በእንስሳት ጤና እና በህብረት ስራ ማህበር ያሰለጠናቸውን የደረጃ አራት ተማሪዎች አስመርቋል።

             

በኘሮግራሙ ላይ የግብርና ሚኒስቴር የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ የኔነሽ ኤጉ፣ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኤክስቴሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀኝአዝማች መስፍን፣ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አህመድ ጋሎ ፣ የኮሌጁ የቀድሞ አመራሮች፣ አጋር የስራ አካላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮሌጁ ለተከታታይ ሶስት ወራት የጽንሰ ሀሳብና የተግባር ትምህርቶችን ለተማሪዎች በአግባቡ በመስጠትና የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የCOC ምዘና በማድረግ  99% በማሳለፍ 903 ተማሪዎችን በዛሬው እለት ለምረቃ አብቅቷል።

ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ካሜራ:- ጌታቸው ታፈረ ( ከክልሉ ግብርና ቢሮ)

ሰኔ 22 /2017 ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

Related

Notices

  • Announcements
  • Vacancy
  • Call For Papers
  • Bids

Downloads

  • Registrar
  • Budget and Finance
  • Policies and Legislations
  • Research and Technology Transfer

Partenerships

  • ARSBA
    Amhara National Regional State Bureau of Agriculture
  • Ministry of Labor and Skills
    Ministry of Labor and Skill
  • wollo unversity
    Wollo Unversity
  • SNV
    SNV Ethiopia
  • giz
    GIZ Ethiopia
  • Smis
    Small and Micro Irrigation Support
Archives