



የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸዉን የደረጃ አራት የደረጃ ማሻሻያ ሰልጣኝ ተማሪዎችን አስመርቋል።
ኮሌጁ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴርና ከአብክመ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ዙር በስድስት የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸዉን 696 የደረጃ አራት የደረጃ ማሻሻያ ሰልጣኝ ተማሪዎችን በዛሬዉ ዕለት በደማቅ ዝግጅት አስመርቋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ የግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን ስራ አስፈፃሚ፣ የአብክመ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ፣ የአፋር /እ/ተ/ል/ቢሮ ሀላፊ፣ የአፋር/እ/ተ/ል/ቢሮ የኤክስቴንሽን ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተርና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች፣ የኮሌጁ አመራሮች፣ መምህራኖች፣ አጋር የስራ አካላትና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የዛሬዉ ቀን የድካማችሁ ፍሬ ያፈራበት የእዉቀት ጉዟችሁ አዲስ ምዕራፍ የያዘበት ታሪካዊ ቀን ነዉና እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ በዛብህ ይመር ግብርና የሀገር ህልዉና የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የነገዉ የብልፅግናችን መሰረት ነዉ ብለዋል።
አያይዘዉም ተመራቂዎች ይህን ታላቅ ተቋም ለቀዉ ሲወጡ የቀሰሙትን እዉቀትና ክህሎት በአፈር ላይ ሂወትን በሀገር ላይ ብልፅግናን እንዲዘሩ አደራ በማለት አሳስበዋል።
በዕለቱ ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫና ሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸዉ ሲሆን ስልጠናዉ የተሳካ እንዲሆን ትብብር ላደረጉ የመንግስት አጋር የስራ አካላት የምስጋና ሰርተፍኬት በማበርከት የዕለቱ መርሀግብር ተጠናቋል።
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ 21/10/2018 ዓ.ም