በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ትምህርት እንድትጀምሩ ጥሪ ለተደረገላችሁ የደረጃ አራት ተማሪዎች በሙሉ
ከየመስሪያ ቤታችሁ ለትምህርት ተመልምላችው በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ የተመደባችሁ የደረጃ አራት ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ፡-
1.ከተላካችሁበት ተቋም የተመለመላችሁበትን ደብዳቤ፣
2.ደረጃ ሦስት ተምራችሁ ያጠናቀቃችሁበትን ሰርተፍኬት፣
3.ከደረጃ አንድ እስከ ሦስት ድረስ ያለውን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣
4.ሁለት 3×4 የሆነ ከለር ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
5.ለግል ማኅደር ማደራጃ አንድ ወፍራሙን ክላሰር በመያዝ በኮሌጁ
ሬጅስትራር ክፍል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆነ እናሳወቃለን፡፡
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ሬጅስትራር