መስከረም 13/2015 ዓ.ም
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ህ/ግንኙነት
ድጋፉ የተደረገው አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ለቃሉ ወረዳ ቀበሌ 034 ለሚገኙና በቀበሌ አስተዳደሩ ለተለዩ የዘማች ልጆችና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 100 ለሚሆኑየአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ነው፡፡
ከድጋፉ ጎን በጎን በቦታው የተገኙት የኮሌጁ ዲን፣ አካ/ምክትል ዲን፣ አስ/ልማት ም/ዲን እና መምህር ዘመነ ሹምየ ለህፃናቱ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቀልፍ መሆኑን ጠቁመው የተሻለ ደረጃ ለመድረስ በትጋት እንዲማሩ ምክር አዘል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የቀበሌው አስታዳዳሪ አቶ ኡመር ታደሠ በኩላቸው ግብርና ኮሌጁ ላለፉት ዓመታትም ከጎናቸው እንደነበረና በርካታ ድጋፍ ማድረጉን አስታውስው ለዚህም ተግባሩ የላቀ ምስጋና ይገበዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ለቀበሌው ት/ቤት የሚውል የጥቁር ሰሌዳ፣ የወንበርና ጠረንጴዛ እንዲሁም የደስክቶፕ ኮ ምፒውተር በኮሌጁ ማኔጅመንት ውሳኔ መሠረት ድጋፍ መደረጉንም የኮሌጁ ዲን በንግግራቸው አሳውቀዋል፡፡
በጥቅሉ በዛሬው እለት ዲጋፍ የተደረጉ ቁሳቁሶች ግምታቸው ከ300 ሽህ ብር በላይ መሆኑን የኮሌጁ አስ/ል/ምክትል ዲን አቶ ዛብህ ይመር በንግግራቸው አሳውቀዋል፡፡
የኮሌጁ አመራርሮችና የስራ ባልደረቦች በመጨረሻም በኮሌጁ የሰርቶ ማሳያ እርሻ ላይ የለሙ የጤፍና የስንዴ
ሰብሎችን ጎብኝተው ተመልሰዋል፡፡