የማትሪክ ተፈታኞች በኮሌጁ ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀመጡ
የማትሪክ ተፈታኞች በኮሌጁ ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀመጡ፡፡
ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም
ኮ/ግኮሌጅ-ህዝብ ግንኙነት
በኮሌጁ ግቢ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮሌጁ ግቢ ውስጥ በዛሬው ዕለት ከጧቱ 1:00 በጀምሮ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡
በተካላው ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ሰይድ፣አካዳሚክ ምክትል ዲን አቶ ውቡ ታየ፣አስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ በዛብህ ይመር፣የውሃ ሀብትና መስኖ ምህንድስና መምህርና የችግኝ ተካላ አስተባባሪ የሆኑት መምህር መከተ አግዘውና ሌሎችም የኮሌጁ የስራ ባልደረቦች፣ ግቢ ውስጥ የነበሩ የፌዴራል ፓሊስ አባላት ተሳትፈዋል