ኮሌጁ የእርሻ ትራክተር ድጋፍ ተደረገለት፡፡
ጥቅምት 9/2015 ዓ.ም
ኮ/ግ/ኮሌጅ-ህዝብ ግንኙነት
ድጋፉን ያደረገው የአብክመ ግብርና ቢሮ ሲሆን ቀደም ሲል አንድ በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጨማሪ ሁለት በድምሩ ሶስት አዳዲስ ትራክተሮች ናቸው፡፡
ትራክተሮቹ ኮሌጁ በኮምቦልቻ መድሃኒአለም እና ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ባሉት የሠርቶ ማሣያ የእርሻ ቦታዎች ላይ የሚያከናውናቸውን የምርምር ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከማሣለጣቸው በዘለለ በዙሪያችን ለሚገኙ አርሶአደሮች የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በስፋት ለመስራት ፋይዳቸው የጎላ መሆኑ በርክክቡ ወቅት ተገልፇል፡፡
ትራክተሮቹ ወደ ኮሌጁ ግቢ ሲደርሱ የኮሌጁ ሀላፊና ምክትል ሃላፊዎች በቦታው በመገኘት ተረክበዋል
በግብርና ቢሮው በኩል ለተደረጉ ድጋፎችም አመስግነዋል፡፡